የጨረታ ማስታወቂያ

የሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ2013 በጀት አመት የሚገለገልበትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ዝርዝራቸው ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው ሰንጠረዥ በተገለፀው መሰረት CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል::

ተ/ቁ የጨረታው አይነት ናሙና /እስፔስፍኬሽን /የሚቀርብበት/  የሚያስይዙት

የCPO መጠን

1 አላቂ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች  ሎት 1 እስፔስፍኬሽን / ናሙና /ይቀርባል 5000
2 ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች  ሎት 2 እስፔስፍኬሽን ይቀርባል 4000
3 ቋሚ የቢሮ እቃዎች /ፈርኒቸር እና ሌሎች የቢሮእቃዎች/ግዥ ሎት 3 እስፔስፍኬሽን ይቀርባል 8000
4 የጥገና እቃዎች ሎት 4 ናሙና ይቀርባል 2000
5 አላቂ የጽ/መሣሪያ ሎት 5 ናሙና ይቀርባል 8000
6 አላቂ የጽዳት እቃዎች ሎት 6 ናሙና ይቀርባል 5000
7 ደንብ ልብስ ሎት 7 ናሙና ይቀርባል 1000
8 የመኪና እቃዎችግዥ ሎት 8 ናሙና ይቀርባል 4000
9 የተለያዩ ህትመቶች ሎት 9 እስፔስፍኬሽን ይቀርባል 1500
10 የመኪና ጥገና ግዥ ሎት 10 እስፔስፍኬሽን ይቀርባል 5000
11 ለቢሮ የሚሆን የህንፃ ኪራይ ሎት11 የተባበሩት አደባባይ (አያት አደባባይ አከባቢ) 3000

 

12 ለቢሮ የሚሆን የህንፃ ኪራይ ሎት12 ጎተራ ማሳለጫ አካባቢ 3000
13 ለቢሮ የሚሆን የህንፃ ኪራይ ሎት13 ከመገናኛ እስከ ሳሊተ-ምህረት ያሉ አካባቢ 3000

በዚህ ጨረታ መሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባችሁ ማስረጃ

1.የንግድ ስራ ፈቃድ በዘመኑ የታደሰ፤ በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገበ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፣ቲን ቁጥር ያለው፣በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው፤ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ የታደሰ ያለው፤የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ /ማስያዝ/ የሚችል መሆን አለበት

2.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለሎት1፣ ለሎት2፣ ለሎት3፣ ለሎት4፣ ለሎት5፣ ለሎት6፣ ለሎት7፣ ለሎት8፣ ለሎት9፣ ለሎት10 እና ለሎት 11 የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር /በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመንጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኤጀንሲው የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 413 በመቅረብ ሰነዱን ገዝተው መውሰድ ይችላሉ::

3.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በሚል በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል::

4.ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በማሸግ የጨረታ ቁጥርና የእቃውን አይነት በግልጽ ፖስታው ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታው  ሣጥን  ውሰጥ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ  ቀናት ውስጥ  በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 413 ማስገባት አለባቸው::

5.ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16ኛው የስራ ቀን በ5:00 ሰአት የጨረታው ሣጥን ተዘግቶ/ታሸጐ/ በ16ኛው ቀን በ5:30 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን  በተመሣሣይ ሰአት ይከፈታል::

  1. ኤጀንሲው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ

የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ሜክሲኮ ጨለለቅ አልሳም ህንፃ 4ኛ ቢሮ ቁጥር 413

ስልክ ቁጥር፡-011-5-53-47-18/ 011-5-58-97-99

አዲስ አበባ