የልምድ ልውውጥ ውይይት ተካሄደ 2

Water And sewrageየፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ከአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከመጡ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር የተሞክሮ ልውውጥ ተካሂዷል፡፡የልምድ ልውውጡ የተካሄደው ሜክሲኮ በሚገኘው በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት የካቲት 29/2009 ሲሆን የኤጀንሲውን የለውጥ እና አገልግሎት አሰጣጥ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለጻና ማብራሪያ ቀረቡት የዋና ዳይሬክተሩ ልዩ ረዳት እና አማካሪ የሆኑት አቶ በጋሻው አየለ ናቸው፡፡በተጨማሪም ስለ(DARIS)Documents Authentication and Registration Information System ገለጻ ያቀረቡት ወ/ሮ ስንታየሁ አበበ የ IT ከፍተኛ ባለሙያ ናቸው፡፡በዚህ በ(Power point) ተደግፎ ከቀረበው ገለጻና ማብራርያ በኋላ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን የኤጀንሲውን የተግባር እንቅስቃሴም ተዘዋውረው እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ ስለተደረገው የልምድ ልውውጥ ኤጀንሲውን አመስግነው የቀሰሙትን ተሞክሮ ወደ ባለስልጣኑ በመውሰድ ተግባራዊ እንደሚያደርጉት ቃል በመግባት የልምድ ልውውጡ ፕሮግራም በዚሁ ተጠቃሏል፡፡በሌላ በኩል በተመሳሳይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬት፤ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን እንዲሁም ከኢትዮጵያ የምግብ የመድሃኒት እና የጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ወደ ኤጀንሲው ለመጡ ሰላሳ /30/ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የካቲት 14/2009 ዓ.ም. በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት የተሞከሮ ልውውጥ ውይይት የተደረገ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

Posted in Uncategorized.